Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዘመን የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ መድኃኒት እና ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዘመን
- የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች
- መድኃኒት እና ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣
1ኛ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የ 2017 ግብር የከፈሉ፡፡
2ኛ –ተጫራቾቹ በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
3ኛ, በገንዘብና እኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የታደሰዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
4ኛ–ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠለት ለመድሃኒት የህክምና መሳሪያ እና ህትመት ግዢ (CPO) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር እና 10,000 (አሥር ሺህ) ብር ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
5ኛ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ አለባቸው ::
6ኛ የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ዋናውን ና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ታሽጎ ነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
7ኛ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን ነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በመቅረብ በባለሙያ ታይቶ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
8ኛ የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጠር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
9ኛ የሚቀርበው ሰነድ ድልዝ ስርዝ መኖር የለበትም ፡፡
10ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶችን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ከነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
11ኛ, ጨረታው የሚከፈተው ከሃያ የሥራ ቀን በኋላ በማግስቱ በ3:00 ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ውክልና ያላቸው ሰዎች አጠገብ በ4፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
12ኛ ተጫራቾች በተጠቀሰው ሰዓት ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
13ኛ ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርበው መሣሪያ ብራንድና ማርኩን ግልጽ አድርጎ በሠነድ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
14ኛ እንደ አስፈላጊነቱ ከተጫራቾቹ አሸናፊ የሆኑ ጋር የውል ስምምነት እስከ ሰኔ 30/2018 ሊቆይ ይችላል፡፡
5ኛ በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የ ጨረታውን ግዴታ ባይወጣ ለውል ማስከበሪያ 10% ያስያዘውን ገንዘብ ለሆስፒታሉ ገቢ ይሆናል፡፡
16ኛ ጨረታውን በክፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብታችን የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0930076418/093076419 አለላቸው
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል