በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት በአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚሰራው ግንባታ ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 001/2018

በኮልፌ ቀራንዮ ከ ከተማ የአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት በአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚሰራ ግንባታ ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

ተ.ቁ

የስራ ቦታ

 

ወረዳ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

 

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

1

አየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚያሰራው የቴራዞ የግንባታ እና ጥገና ስራዎች

04

ለደረጃ GC7/BC 6 እና ከዚያ በላይ 60,000 ብር

ደረጃ GC7/BC 6 እና ከዚያ በላይ የሆነ ተቋራጭ

90 ቀን

 

 

1. ለስራው የንግድ ምዝገባ እና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑ ግብር የ2016 ዓ/ም የከፈሉ፣የ2017 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ውረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ከገቢዎች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት መዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው

2. ተጫራቾች የጨረታ ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ፊርማ ማህተም እና የሚወዳደረበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋ በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሽያል በአንድእናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፊርማ እና የሚወዳደርበትን የፕሮጀክት ስም በመፃፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀስው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናሉ።

3.ተጫራቾች ጨረታውን በጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:00 ድረስ በከልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ አስተዳደር አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት በቁጥር የተጠቀሱትን ማስረጃቸውን ኦርጂናል (original) እና የማይመለስ ኮፒይዞ (copy) በመቅረብ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር)ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 10 የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን ጠዋቱ 4፡30 ድረስ በኮለፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 11ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

4. ተጫራቾች በ 90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or SECURITY) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ውይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (UNCODILONAL BANK  GUARANTEE) በኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለበት።

5. ተጫራቾች በጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚስራውን ስራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቾቹ የዋጋ ትንታኔ (COSI BREAK DOWN) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ (UNVALANCED RATE ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል።

6. ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሽያል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድለዝ (unsigned rate correction) እና ነጠላ ዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for rate correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ይሰረዛል።

7. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነፃ እንደሚሰራ ይወስዳል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መጠሪያን በሚያዝዘው መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ከሚሰራው ስራ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ከመንግስት ተቋማት ማቅረብ የሚችሉ።

የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፦ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት

አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት

ልክ:- 011 835 7496/ 011 883 87908

ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *