Your cart is currently empty!
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ኩባንያ ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ብዛት ያላቸውን ዘይቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
2merkato.com(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ቀን፡- ነሐሴ13፤2017 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ብዛት ያላቸውን ዘይቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የእቃዎቹ ዓይነት ከነብዛታቸው እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡
ተ.ቁ |
የዘይቱ አይነት |
ብዛት |
1 |
DELO GOLD ULTRA 15W40 25L |
53 |
2 |
HAVOLINE FORMULA 20W50 1L |
287 |
3 |
HAVOLINE FORMULA 20W50 4L |
8 |
4 |
TEXACO CETUS PAO 68 18.9L |
1 |
በመሆኑም ኩባንያችን ከላይ የተጠቀሱትን ዘይቶች ባሉበት ሁኔታ ለእያንዳንዱ ዋጋ በመስጠት ማወዳደርና መሸጥ ይፈልጋል። እቃዎቹን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ኖክ ቃሊቲ መጋዘን ተገኝተው በመመልከት የእያንዳንዱን የዘይት ዓይነት ባሉበት ሁኔታ የሚገዙበትን ዋጋ 15 በመቶ ቫትን ጨምሮ በመግለጽ ኩባንያው ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርብዎታል። ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200.000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሊፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይችላል፡፡ በተጨማሪም ተጫራች ለጨረታ የተዘጋጀውን ፎርም ቦሌ ፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው የኖክ ህንፃ (13ኛ ፎቅ) ለመውሰድ ሲመጡ የታደስ የንግድ ፍቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርብዎታል።
አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለጸለት ገንዘቡን በአንድ ጊዜ ክፍያ ይፈፅማል። ይህ ሳይሆን ሲቀር ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል። አሸናፊው እቃዎቹን በአስር ተከታታይ ቀናት ከኖክ ቃሊቲ መጋዘን ማንሳት አለበት ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 5,000.00 ብር ይከፍላል። ሙሉ ክፍያ ሲፈጽም ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል፡፡
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋ/መስሪያ ቤት
ስልክ፡- 011-6-18-71-65 ወይም 011-4-39-03-78
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ኩባንያ