Your cart is currently empty!
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ኩባንያ (ኖክ) ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ብዛት ያላቸውን ባዶ የዘይት መያዣ ጀሪካኖችን ባሉበት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
2merkato.com(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ቀን፡- ነሐሴ 13፧2017 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ብዛት ያላቸውን ባዶ የዘይት መያዣ ጀሪካኖችን ባሉበት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የእቃዎቹም ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
ተ.ቁ |
የባዶ የዘይት መያዣዎች ዓይነት |
ብዛት |
1 |
1 ሊትር ጀሪካን |
15 |
2 |
5 ሊትር ጀሪካን |
4 |
3 |
20 ሊትር ጀሪካን |
2 |
4 |
25 ሊትር ጀሪካን |
4 |
ጠቅላላ |
25 |
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ባዶ የዘይት መያዣ ጀሪካኖችን ባሉበት በጥቅል ዋጋ በመስጠት ማወዳደርና መሸጥ ይፈልጋል፡፡ እቃዎቹን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ኖክ ቃሊቲ መጋዘን ተገኝቶ በመመልከት በጥቅል የሚገዙበትን ዋጋ ከ15 በመቶ ቫት ጋር በመግለጽ ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ እንዲሁም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ) ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይቻላል፡፡
አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለጸለት ገንዘቡን በአንድ ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ይህንን ባይፈጽም ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡ አሸናፊው እቃዎቹን በአስር ተከታታይ ቀናት ከቃሊቲ መጋዘን ማንሳት አለበት፡፡ ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 1,000.00 ብር ይከፍላል፡፡ ሙሉ ክፍያ ሲፈጽም ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁ. 011-6-18-71-65 ወይም 011-4-39-03-78 መደወል ይቻላል።
አድራሻ:- ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋ/መስሪያ ቤት
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ኩባንያ (ኖክ)