ወሳሳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በዱከም ክ/ከተማ ላስገነባው B+G+5 ህንፃ ለቀሩት የፊኒሽንግ ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

ወሳሳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በዱከም ክ/ከተማ ላስገነባው B+G+5 ህንፃ ለቀሩት የፊኒሽንግ ስራዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ዝርዝር ሥራውና መግለጫው በተገለፀው መሠረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም፦

  1. ህጋዊ የታደሠ የንግድ ፈቃድ እና የተሰማሩበት ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2.  ህጋዊ የምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ህጋዊ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበበትን ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ህጋዊ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ የታደሠ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡
  6. ደረጃ GC/BC_5 ወይም ከዚያ በላይ ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  7. ለጨረታ ሲመጡ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ/ ብር በወሳሳ ማይክሮ ፋይናንስ ስም የተዘጋጀ CPO ማቅረብ አለበት።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 ብር /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ በወሳሳ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን Technical እና Financial ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 03/13/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ድረስ በወሳሳ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው 03/13/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  12. ወሳሳ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፦ ሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከ ጨ/ከራቡ ወረዳ ልዩ ቦታ ኮንዶሚየም ጀርባ ሶስና ት/ቤት መሄጃ የባቡር ሀዲድን ሳይሻገር

ስልክ ቁጥር 0113384133/0912292397

ወሳሳ ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *