Your cart is currently empty!
ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን የጠላቂ ፓምፕ እና የተለያዩ ኤሌክትሪካል እቃዎች አቅርቦት፣ የSolar Components አቅርቦትና የተከላ ስራ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ ያካተተ እና የአሽዋ መፍጫ ማሽን አቅርቦትና የተከላ ስራ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ ያካተተ /ለአጅማ ጫጫ ፕሮጅከት/ ግዥ ለመፈፅም በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ተጫራቾች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- NCB WWC 01/2018
የውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የክልሉን የውሀ ሀብት በማልማትና ለንፁህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፣ ቁፋሮ ፣ ዘመናዊ መስኖ ግድብና ጠለፋ ስራዎችን በመስራት የክልሉን ብሎም የአገሪቱን እድገት ለማፍጠን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ ለምስራቅ ጎጃም ዞን ሽበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ ለገዳ እያሱ ወይንየ እና ሞጃሆን መጠጥ ውሃ እና አጅማ ጫጫ ፕሮጅክት ስራ አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 የጠላቂ ፓምፕ እና የተለያዩ ኤሌክትሪካል እቃዎች አቅርቦት
- ሎት -2- የSolar Components አቅርቦትና የተከላ ስራ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ ያካተተ እና
- ሎት 3 የአሽዋ መፍጫ ማሽን አቅርቦትና የተከላ ስራ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ ያካተተ /ለአጅማ ጫጫ ፕሮጅከት/ ግዥ ለመፈፅም በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ተጫራቾች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሆነ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው
- ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ከቴክኒካልና ፋይናንሻል ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ፤ የተጫራቾች መመሪያ ፣ የቴክኒከ መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00( አምስት መቶ ብር) ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሬስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማሳሰቢያ፡- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጅ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- ተጫራቾች በኮርፖሬሽናችን ስም የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድቦንድ/ ሎት -1 እና ሎት 2 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ሎት 3 250,000.00 /ሁለት መቶ አምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ለ9ዐ ቀናት እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን ጠቅሰው በታሸገ ፖስታ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል ከሚያሳይ ማኑፋክቸረር ብሮሸር(Original Manufacturer Brusher) ጋር ለየብቻ በማሸግ ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ያስገባሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀን አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት በ8፡30 የሚከፈትይሆናል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከናወናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ9ዐ ቀናትና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን በመረዳት የጨረታ ዋጋ በውል ዘመኑ በሙሉ የፀና መሆን ይኖርበታል ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን ለማቅረብ ቅድሚያ ክፍያ የሚጠይቅ ከሆነ ከተከፈለው ቀን ጀምሮ የሚታሰብ በ60 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡ ኤልሲ (C) ወይም ሌተር ኦፍ ክሪዲት እንደ መስፈርት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ በተገለጸለት በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ክፍያን በተመለከተ ደግሞ 30% ቅድሚያና 70% ርክክብ ሲፈፀም የሚከፈልይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታከስ ፣ የትራንስፖርት ፣ የማስጫኛ ፣ የማራገፊያ ዋጋም ጨምሮ ምስራቅ ጎጃም ዞን ሽበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ ለገዳ እያሱ ወይንየ እና ሞጃሆን መጠጥ ውሃ ፓሮጅከት፣ ሎት ና 2 እና አጅማ ጫጫ ፕሮጅክት /ሎት-3/ ንብረት መጋዝን ማውረድ ድረስ በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ በግልፅ በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው የተዘረዘሩ የንብረት አይነት እና መጠን በእያንዳንዱ ሎት መወዳደር ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን በእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ድምር የሚወዳደሩ ይሆናሉ ፡፡
- የፋይናንሻል ጨረታው መክፈቻ ቀን በቴክኒካል ለተመረጡ ብቻ በደብዳቤ ይገለፃል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ በዋና መ/ቤት ቢሮ ባህርዳር ግዥ ክፍል 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር- 058 222-14-79 መጠየቅ ይችለሉ፡፡
ቀበሌ 14 አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን