Your cart is currently empty!
የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ያለውን የማኅበሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ፈቃድ ባላችው የሂሳብ ባለሙያዎች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 18, 2025)
Please read the detailed instructions below.ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር የኦዲት ሥራ
የጨረታ ማስታወቂያ
የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ያለውን የማኅበሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ፈቃድ ባላችው የሂሳብ ባለሙያዎች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ማኅበሩን ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃዱን ያሳደሰች።
- በሂሣብ ምርመራ ኦዲት ተግባር ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት፣CV /የትምህርት ደረጃ ፣ የሥራ ልምድ ወዘተ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተያዘ /የተገባ/ የቅጥር ውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ።
- የበጀት ዓመት (ቶች) ሂሣብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ሁለት በመቶ “በመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር” ስም ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያከናውኑትን ተግባር በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ሊሆን ይገባል።
- ከተቻለ ተጫራቾች ስለመልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድርጀቶች የተፃ ላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት (ተመዝጋቢ ከሆነ)፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት /ቲን/ እና ሌሎች ሕጋዊ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን በጀት ዓመት ኦዲት ሥራ፤ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትን የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ (ከነሐሴ 12/2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 22/2017 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፤ ሳርቤት አካባቢ በሚገኘው መቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች(ኮንዶሚኒየም) ግቢ፤ የማኅበሩ ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላትና በኤንቨሎፕ በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር – +251911901971/+251924241388 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር