Your cart is currently empty!
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ዞኖች ለመተከል ዞን፤ አሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን ውስጥ ለመንገድ ከፈታ እና መንገድ ጥገና ሥራ ላይ የሚሠማሩ ማሽኖችን ለመከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቀጥር 01/2018
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ዞኖች ለመተከል ዞን፤ አሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን ውስጥ ለመንገድ ከፈታ እና መንገድ ጥገና ሥራ ላይ የሚሠማሩ ማሽኖችን ማለትም ዶዘር ብዛት 03፣ ግሬደር ብዛት = 03, ሩሎ ብዛት = 03 ሎደር ብዛት = 03, ገልባጭ መኪና ብዛት= 09, ትንሽ መኪና ዳብል ጋቤና ብዛት= 04, ውሃ ቦቴ ብዛት 03, ኤክስካቫተር ብዛት 03, ሎቤድ ብዛት=01 በግልጽ ጨረታ ለመከራየት ይፈልጋል:: አንዱን ዶዘር በሰዓት ሂሳብ ለ1500:00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት)፤ አንዱን ግሬደር በሰዓት ሂሳብ ለ1500:00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት) አንዱን ሎደር በሰዓት ሂሳብ ለ1500:00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት)፤ አንዱን ሩሎ በሰዓት ሂሳብ ለ1500፡00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት)፤ አንዱን ገልባጭ መኪና በቀን ሂሳብ ለ160 ቀናት፤ አንዱን የትንሽ መኪና ዳብል ጋቤና በቀን ሂሳብ ለ160 ቀናት፤ አንዱን የውሃ ቦቴ በቀን ሂሳብ ለ160 ቀናት፤ አንዱን ኤክስካቫተር በሰዓት ሂሳብ ለ1500:00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዓት)፤ አንዱን ሎቤድ በአንድ ኪ.ሜትር ሂሳብ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፣
በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በ2018 በጀት ዓመት ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላችሁ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገባችሁ መሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ድረ ገጽ መግለጽ የሚችሉ፤
- የሚያከራዩን መሳሪያዎች የራሳቸው ለመሆኑ የባለቤትንት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም አግባብ ባለው ሙሉ የህግ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ
- የድርጅታቸውን (የቢሮዋቸውን) አድራሻ ማሳየት የሚችሉ የሆኑ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መውስድ ይችላሉ::
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት (አስራ አምስት) ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛ ቀን) ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የፋይናንስና የቴክኒክ ዶክመንት ለየብቻው በማድረግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ተዘጋጅቶ በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የሚያከራዩትን ማሽኖች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) ኮፒውን እና የውክልና ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) አሳይተው ካስመዘገቡት ማሽን ውጭ ጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ቢያቀርቡ _ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በተመለከተ፤ ለአንዱ ዶዘር ብር 40,000.00 / አርባ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ግሬደር ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ሎደር ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ሩሎ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ገልባጭ መኪና ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር ፤ ለአንዱ ትንሽ መኪና ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ውሃ ቦቴ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/፤ለአንዱ ኤክስካቫትር ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/፤ ለአንዱ ሎቤድ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/፤ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ ለብቻው በማሸግ (ከፋይናንሻል ዶኩሜንት ወይም ከቴክኒካል ዶኩሜንት ጋር መታሸግ የለበትም) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው:: በመሆኑም ከባንክ ከተረጋገጠ CPO ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ማሽነሪ እና ተሽክርካሪ አይነት ከተጠየቀው ብዛት ውጭ መወዳደር አይቻልም።
- መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የስልክ ቁጥር ፡-057 775 2622
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ
አሶሳ