የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ ማሻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሚያከናውነው የመንገድ ስራ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ ማሻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሚያከናውነው የመንገድ ስራ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በድጋሚ በወጣ ጨረታ ቁጥር 002 አወዳድሮ ለመከራየት ስለፈለገ ከታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ መከራያት ይፈልጋል።

/

Description

1

 

Pick-up Double Cabin, Diesel Engine Minimum Capacity 2.4L with D4D Turbo Charger model Above 2010 Good condition

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን ሁኔታ በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል።

  1. በ 2017 ዓ.ም ለዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና ከገቢ ግብር እዳ ነጻ ማስረጃ ጨረታው እስከሚገባበት ቀን የሚያገለግል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ነሃሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ዲሪ ማሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከሚገኘው የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሎት በመግለጽ ተዛማጅ ማስረጃቸውን ሁሉንም ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥኑ ውስጥ የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ነሃሴ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ብቻ ነው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነት በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም።
  5. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅጽ ሞልተውና ፈርመዉ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ለማቅረብ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
  6. የጨረታ ሳጥኑ ነሃሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 በግዢ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ
ስልክ ቁጥር 0910 00 90 79
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዲሪ-ማሻ መንገድ ፕሮጀክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *