Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሆሮሬሳ, ሻላ ቢላ ቀበሌ, አርሲ ነገሌ ወረዳ ምዕራብ አርሲ ዞን, ኦሮሚያ ክልል የ kindergarten KG (የህጻናት ትምህርት ቤት) ዲዛይን ክለሳና ግንባታ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– SSNT-T561
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሆሮሬሳ, ሻላ ቢላ ቀበሌ, አርሲ ነገሌ ወረዳ ምዕራብ አርሲ ዞን, ኦሮሚያ ክልል የ kindergarten KG (የህጻናት ትምህርት ቤት) ዲዛይን ክለሳና ግንባታ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። ድርጅቱ በ 270 ቀናት ውስጥ ሥራውን ሰርተው ማስረከብ ከሚችሉ ድርጅቶች ተዋውሎ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ኃይል እና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ ለመስራት ለ2017 ዓ.ም ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
- በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ 2017 ዓ.ም የታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC BC 5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያለው።
- የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና በኢ.ፌ.ድ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢ እና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T561 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ። በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት(ስራ) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት አሮጊው የሰው ሀብት ህንፃ አጠገብ በሚገኘው የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-57 4552
ወ/ሮ ብርትካን ሰሙ
ኢሜይል: BirtukanS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።