Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት፣ የአትዮጵያ አቬሽን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የመማሪያ ክፍል እና ዋና በር፣ በጂጂጋ ኤርፖርት የመምህራን መኖሪያ፣ ካፍቴሪያ፣ የግቢ አጥር፣ የመዳረሻ መንገድ፣ የግራውንድ ቴኒስ ኮርት ሜዳ እና የመሬት አቀማመጥ ስራ ፕሮጀክት ለዲዛይን ክለሳ፣ ለግንባታ ቁጥጥር እና ለኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T562
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት፣ የአትዮጵያ አቬሽን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የመማሪያ ክፍል እና ዋና በር፣ በጂጂጋ ኤርፖርት የመምህራን መኖሪያ፣ ካፍቴሪያ፣ የግቢ አጥር፣ የመዳረሻ መንገድ፣ የግራውንድ ቴኒስ ኮርት ሜዳ እና የመሬት አቀማመጥ ስራ ፕሮጀክት ለዲዛይን ክለሳ፣ ለግንባታ ቁጥጥር እና ለኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ (Category | (One) local and International Consultant for the Design Review, Construction Supervision and Contract Administration for Classrooms, associated facilities and Main Gate projects for EAU at Addis Ababa Bole International Airport and Dormitory for Instructors, Cafeteria, Compound fence, Access Road, Ground Tennis Court and Landscaping work projects at Jigjiga Airport) ደረጃ አንድ የማማከር ፍቃድ ያላቸውን የሀገር ውስጥና እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡–
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ለ2017/2018 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የTIN (የግብር ከፋይ) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ VAT (የተጨማሪ እሴት ግብር) ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታከስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካልለ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ በሲቪል ምህንድስና የማማከር ፍቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T562 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች ወይም እኩሌታ በአሜሪካን ዶላር ለአለም አቀፍ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብና ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን(ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የቀድሞ የሰው ሀብት አስተዳደር በጨረታ መክፈቻ ክፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ሰላም ገዳሙ
ስልክ ኢሜይል፡ SelamGe@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡