Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተሽከርካሪ ነዳጅ እና የተለያዩ የመኪና ቅባቶችን ለዋናው መሥሪያ ቤት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T562
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተሽከርካሪ ነዳጅ እና የተለያዩ የመኪና ቅባቶችን ለዋናው መሥሪያ ቤት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የንግድ ምዝገባ ምዝገባ ምስክር ወረቀት/TIN/ ያላቸው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በነዳጅና አቅራቢነት ህጋዊና የታደሰ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T562 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል እስከ ጳጉሜ 03 ቀን 2017 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡
ቦሌ አlም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-89-18
ኢ–ሜይል: ESAYASIS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Ethiopian