የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የተለያዩ 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የተያዩ 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

(ቁጥር ግልድ 03/2018)

1.የጨረታ ማስታወቂያ፡

ድርጅታችን ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፀውን ጥራት ያለው 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርፍትኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።

2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች አስፈላጊውን ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ጥራት ያለው 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት በጨረታው ላይ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።

4. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ ፊት ለፊት ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 200 – 630 እንዲሁም አርብ ከጠዋቱ 200-530 ከሰዓት 730 – 1100 ሰዓት መወስድ ይችላሉ።

5. በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ስም የተዘጋጀ የብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ለብቻው በታሸገ ኢንቮሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ማወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች ጋር በታሸገ ኢንቮሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ስዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማቅረብ ይችላሉ።

7. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ነሐሴ 22 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 410 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 369-2243 / 011 369-1886

www.eiide@eiide.com.et


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *