Your cart is currently empty!
የካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አብዮት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቀዎች፣ ህትመት፣ የት/ት ዕቀዎች፣ ጽዳት ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች እና የውሃና ቆሎ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– የካ/አብ/30/114/2017
የካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አብዮት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት 1ኛ ዙር በ2018 በጀት ዓመት ህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ የሚከተሉትን ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 – የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 – አላቂ የቢሮ ዕቀዎች፣
- ሎት 3 – ህትመት፣
- ሎት 4 – የት/ት ዕቀዎች፣
- ሎት 5 – ጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 6 – ልዩ ልዩ መሳሪያ፣
- ሎት 7 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት 8 – የቢሮ ዕቃዎች እና
- ሎት 9 – የውሃና ቆሎ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዢ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቀባቸውን ዕቃዎች መጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበትን ናሙና የማስገባት ግደታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 – 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 – 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 3 – 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 4 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 5 – 5,000 (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 6 – 3,000 ብር (ሶስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 7 እና 8 ለእያንዳንዳቸው 4,000 ብር (አራት ሺህ ብር)፣ ለሎት 9 – 4,000 ብር /አራት ሺህ ብር/ በየካ ክ/ ከተማ ት/ጽ/ቤት አብዮት የመ/ደ/ት/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ከኦሪጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ከታወቀ በሀዋላ ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋው 10% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ክፍል 4 እና ክፍል 5፣ 6 በሚገባ በሙላት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦሪጅናል እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- መ/ቤቱ እቃዎችን በጨረታ ሰነድ ከተጠቀሰው መጠን 20% መቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብዮት የመ/ደ/ት/ቤት በሚገኘው የግ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ በ11ኛው ቀን ማስገባት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባችኃል፡፡ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆንና አለመሆኑን ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 09-22-82-62-84 ወይም 09-31-56-70–71
መቶ ብር/ አድራሻ፡– መገናኛ ለም ሆቴል አጠብ ከኖክ ሚደያ ጎን በሚገኘው አብዮት የመ/ደ/ት/ቤት
አብዮት የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስና የግዢ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በየካ ክ/ከ/ትምህርት ጽ/ቤት የአብዮት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Materials cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Promotional Items cttx, Electromechanical and Electronics cttx