Your cart is currently empty!
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማዎች ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማዎች ግዥ ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 01/2018
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሎት አንድ ለከባድ ተሸክካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማዎች ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፤ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላለቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸውን፣ የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ የቴክኒክ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሽገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለየ ፖስታ በማድረገ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በትክክል ማስፈር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያውኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይክፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች በእንግሊዘኛ የተጻፈውን የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ በሚጠይቀው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ያልሞሉት የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ የማቅረብያ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት፤
|
ሎት አንድ
|
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
1 |
12.000R22.5
|
200,000.00
|
2 |
12.00R24.00
|
400,000.00
|
የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም ከኢሹራንስ ዋስትና ወይም ከኢንሹራንስ ዋስትና በቀር በግዥ መመሪያው ላይ ባሉ አማራጮች በፈለጉት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋለ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳሉ፡፡ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
9. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከተፈተ በኋላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
10. ባለሥልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት መሆኑ ከተገለፀለት አምስት /5/ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና (Performance Bond) 10% በባንክ በጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈራረም ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
ስልክ ቁጥር፡- 09 23 69 00 58/ 09 16 86 62 62
ዲላ/ኢትዮጵያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት መንገዶች ባለሥልጣን