Your cart is currently empty!
ደ/ማ/አስ/ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Addis Zemen(Aug 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ ባንቻየሁ ይታየው የአፈ/ተከሳሽ የ፻ አለቃ ይረፉ ቤዛ መካከል ስላለው የአፈ/ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሳሽ ፻ አለቃ ይረፉ ቤዛ ስም በደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 09 ክልል የሚገኝ 150 ካ.ሜትር ቦታ ላይ የተሰራ መኖሪያ ቤት የካርታ ቁጥር K/አብ 2930 የሆነ አዋሳኙ በምስራቅ ዘሩ አባተ፣ ምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ዘውዱ ባንተአምላክ፣ በደቡብ ተፈራ አይተነው የሚያዋስኑት የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,409,257 /አንድ ሚሊየን አራት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሰባት ብር/ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ የሚወጣበት ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ማስታወቂያ ለአንድ ወር በአየር ላይ ውሎ ጨረታው መስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ በጨረታ ይሸጣል ፡፡
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰውን የመኖሪያ ቤት በጨረታ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በሰዓቱ በመገኘት መጫረት የሚችሉ ሲሆን ወደ ጨረታ ለመግዛት በመጀመሪያ ደረጃ የጨረታ መነሻ ዋጋ 25 % CPO ማንኛውም ህጋዊ በሆነ ባንክ በማስያዝ ያስያዙበትን ደረሰኝ (ሪሲት) በእለቱ ለሀራጅ ባይ በማስያዝ ሲጫረቱ ከዋሉ በኋላ የጨረታ አሸናፊ መሆኑ እንደታወቀለት ደግሞ የሽያጩን ጠቅላላ ገንዘብ 75 % CPO ወዲያው ማስያዝ አለባቸው ካላስያዙ ካስያዙት ገንዘብ ላይ ለጨረታ ማስፈፀሚያ የወጣ ልዩልዩ ወጭዎች ተቀንሶ ቀሪው ለመንግስት ገቢ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ደ/ማ/አስ/ፍ/ቤት
ደ/ማርቆስ