ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ሚድ ባስ፣ ዳብል ጋቢና ተሽከርካሪ እና ባጃጅና ሞተር ሳይክል እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት የተዘጋጀ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር ግ/ላ/ኢ/01/2018

ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

  • ሎት 1 ፤ ሚድ ባስ
  • ሎት 2 ፤ ዳብል ጋቢና ተሽከርካሪ
  • ሎት 3 ፤ ባጃጅና ሞተር ሳይክል እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ወይም በማህበራት የተደራጁ ከሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ሀላፊ ፊርማ የተፃፈ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ኦርጂናል ዶክመንትና ኮፒ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የግዢውን ብር 2% ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋማቱን ከአደራጀው ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ስራዎች ማስፋፊያ ጽ/ቤት ብቻ በጽ/ቤት ሀላፊው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ቡና ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ 300 ብር በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ 16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ጀምሮ አዲስ አበባ 22 ፍትህ ሚኒስቴር የስብሰበ አዳራሽ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀናት ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ይሆናል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለበት፤ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበው ዋጋ ቫትን አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
  6. ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 20 47 80 39 /09 13 07 25 07 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *