ሀዛል ሪል እስቴት አ.ማ የ2017 በጀት አመት ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የውጭ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

ማህበራችን ሀዛል ሪል እስቴት አክሲዮን ማህበር በብር 500,000,000 አምስት መቶ ሚሊዮን) የተመዘገበ ካፒታል ተመስርቶ መርካቶ /ሲኒማራስ/ አካባቢ በሁለት ሳይቶቹ ላይ የሪል እስቴት ልማት በማከናወን ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው:: እስከ 2016 በጀት አመት ኦዲት አስደርጎ ያጠናቀቀ ሲሆን በተመሳሳይ የ2017 በጀት አመት ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ኦዲተር ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 6 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ማቅረብ ይኖርበታል:: ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል በሚል ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በተጨማሪም የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ: የታደሠ የሙያ ፈቃድ : የግብር ከፋይ መለያ እና የተ.እ.ታክስ ሠርተፍኬት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: የዘመኑን የሠነድ ብዛት 10 ቦክስ ፋይል ሲሆን በአካል ማየት ለሚፈልጉ በሳይቱ በሚገኘው ቢሯችን 2ኛ ፎቅ በመምጣት መመልከት ወይም በስ.ቁ. 0904 673 222 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::

ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ሀዛል ሪል እስቴት አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *