በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የኤሌክትሪክ ኬብል ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

 ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2017 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ኬብል ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ሎት 1 የኤሌክትሪክ ኬብሎች

መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin No / ያላቸው፣
  6. በመንግሥት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረገጽ (WWW.PPA.gov.et)
  7. ተጫራቾች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ ሀ. ሎት 1 የኤሌክትሪክ ኬብሎች 100,000 ብር (CPO)
  8. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዝ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ ለሚወዳደሩበት እቃ በእስፔስፊኬሽኑ መሰረት መሆን አለበት፣
  10. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15 ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 200 ብር/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  11. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
  12. /ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣
  13. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሽያል ኦርጅናል በአንድ ፖስታ እና ኮፒ አንድ ፖስታ ከዚያ ደግሞ ቴክኒካል ኦርጅናል በአንድ ፖስታ እና ኮፒ በአንድ ፖስታ ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ሕንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15 ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፤
  14. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ 
    ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፣ 
    ለ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፤ 
  15. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣
  16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ 8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፣
  17. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ይከፈታል። ነገር ግን ከ11ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡

1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን /ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።

2. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ፣ 1 ፒያሳ) እስታቲክስ ጎን እናት ሕንጻ ፊት ለፊ ዋስትና ንግድ ማእከል 15 ፎቅ ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-127-6825 ይደውሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *