Your cart is currently empty!
በደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ለ2018 በጀት ዓመት በመንግስት ከሚበጅትልን መደበኛ በጀት ላይ በሚማው መሠረት ለአካዳሚው ሠልጣኞች በሜኑ መሠረት የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች አዘጋጅቶ ለ/1/ አንድ ዓመት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመመገብ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ለ2018 በጀት ዓመት በመንግስት ከሚበጅትልን መደበኛ በጀት ላይ በሚማው መሠረት ለአካዳሚው ሠልጣኞች በሜኑ መሠረት የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች አዘጋጅቶ ለ/1/ አንድ ዓመት የሚቆይ ከዚህ በታች በሎት በተዘረዘረው መሠረት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመመገብ ይፈልጋል፡፡
በሎት አንድ በሚማው መሠረት ለአካዳሚው ሠልጣኞች በሜኑ መሠረት የተለያዩ የምግብ አይነቶች አዘጋጅቶ ማቅረብ።
በዚህ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመጫረቻ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር የከፈለበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin number) ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ወይም TOT ተመዝጋቢ የሆነ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /C.PO/ወይም በሌተር ኦፍ ክሬዲት ማቅረብ የሚችል፤
- ከክፍያው 3% ተቀናሽ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታውን ተወዳድሮ ሲያሸንፍ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /C.PO/ ወይም በሌተር ኦፍ ክሬዲት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች መገምገሚያ ሰነዱን መ/ቤቱ በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት ተፈርሞበት እና በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ መቀመጥ አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱ ሁለት /2/ ፖስታ ማለትም በኦርጅናል እና በኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ በመቅረብ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ በኤንቬሎፕ በማድረግ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ ይዘው ሲያቀርቡ የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻ በማድረግ የተለያዩ ሁለት /2/ ፖስታ በሰም በታሸገ በኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16 ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ በመጀመሪያው የሥራ ቀን ወይም ሰኞ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል በመግባት ያሸነፈውን ለአካዳሚው ሠልጣኞች በሜኑ መሠረት የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች በማዘጋጀት በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ አማን ድረስ አምጥቶ የማቅረብና የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው እና ውል ማስከበሪያ ተብሎ ያስያዘው /C.P.O/ ውርስ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የጨረታው እና ውል ማስከበሪያው በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በሌተር ኦፍ ክሬዲት ብቻ መቅረብ አለበት፡፡
አድራሻ ፡- ሚዛን – አማን
በደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ