Your cart is currently empty!
ተስፋ ድርጅት በኦሮሚያ ክልል በዝዋይ ዱግዳ ሂራራ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 250 ተማሪዎች ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Reporter(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የምግብ አቅርቦት
የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት በሲቨል ማህበራት ኤጄንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት ይሰጣል። ድርጅቱ ለሚረዳቸው ተማሪዎቹ፤
1. በኦሮሚያ ክልል በዝዋይ ዱግዳ ሂራራ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 250 ተማሪዎች ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ቅጽ ሰነድ ከተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሃሴ 28 ቀን 2017 ከቀኑ 6.00 ሰአት ድረስ ማስገባት እንደምትችሉ እናስታውቃለን።
ጨረታው ነሃሴ 28 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራጮች ለአንድ የትምህርት አመት ባቀረቡት ዋጋ ምግቡን የማቅረብ ሀላፊነት አለባቸው።
ከአማካይ ምግብ ዋጋ በጣም ዝቅተኛ ወይም በጣም ከፍተኛ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ሊያሰርዙ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ፡– አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤ/ት አየር ጤና፣ ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 011 348 2537 የመሳጥን ቁጥር 30153 አዲስ አበባ
ድርጅቱ