አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰሀላ መሻህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል Sand filter media (silica sand, sand medium course, quartzite gravel) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አኮኃ/ብግጨ/11/17

አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰሀላ መሻህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል Sand filter media (silica sand, sand medium course, quartzite gravel/ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ድርጅቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 16 ህዳሴ ሰፈር ፊት ለፊት አመልድ ጋራጅ ውስጥ ከሚገኘው አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ከግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት በስራ ሰዓት ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል፤ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል።
  7. 10ኛው ተከታታይ ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 91 02 14 30 በመደወል ወይም በድረ-ገጻችን https://www.abay-construction.org.et/auction-bid/  ላይ ማግኘት ይችላሉ።

አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *