Your cart is currently empty!
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች የተለያዩ የማሽነሪ እና የተሽከርካሪዎች ጎማ እና ባትሪ፣ ዘይትና ቅባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2018
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች
- 1ኛ/የተለያዩ የማሽነሪ እና የተሽከርካሪዎች ጎማ እና ባትሪ ሎት 1
- 2ኛ/ዘይትና ቅባት ሎት=2 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ፡–
1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በበጀት ዓመቱ የንግድ ፈቃዳቸው የታደሠ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
2. በመስኩ ስራ ላይ ለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሠነድ የያዘ ዶክመንት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አሶሳ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
3. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአሶሳ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል።
4. የጨረታው መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ እና በማሸግ አሶሳ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል ሠነዱን ይዘው በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብን በተመለከተ 1ኛ/ የተለያዩ የማሽነሪ እና የተሽከርካሪዎች ጎማ እና ባትሪ፣ የባትሪ አሲድና የባትሪ ውሃ ፤ሎት=1 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ 2ኛ/ የዘይትና ቅባት ሎት 2 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ/ በመ/ቤታችን ስም በተዘጋጀ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው ። በካሽ /በዋስትና ደብዳቤ/ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ (ጠቅላላ ዋጋ) ስርዝ ድልዝ እና በእርሳስ የተሞላ ሠነድ ተቀባይነት የለውም። የሚቀርበው ዋጋ ከ15% ቫት ጋር ወይም ከ15% ቫት በፊት ተብሎ በግልጽ ተጽፎ መቀመጥ አለበት ይህ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ኮፒውን ይዘው ማቅረብ አለባቸው።
9. የዕቃዎች መረካከቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሆኖ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል።
10. መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 057 775 2622 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የቤ/ጉ/ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ
አሶሳ