Your cart is currently empty!
የቦታው ስፋት 179 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ድጋሚ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ዘውድነሽ እንዳለ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አገሪቱ ኃ/ማሪያም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.100983 በቀን 27/6/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ.102040 በ10/7/2017 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የቤ.ቁ 137 የሆነ ቤት ፍርድ ያረፈበት የካርታ ቁጥር 3/79/34304/00 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 179 ካ/ሜ LDP ላይ ያለ በመንገድ ጥናት መሰረት ከይዞታው 83 ካ/ሜ የሚነካው ሲሆን ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,986,204 (አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ሲሆን በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ በመሆኑም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.102040 በቀን 08/12/2017 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.428 መሰረት ድጋሚ የሐራጅ ጨረታ የግምቱ 1/4ኛ 1,996,551 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ አንድ) ሆኖ መሰከረም 15 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/ኢዳ ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው እካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት