Your cart is currently empty!
የተለያዩ የጥርስ ህክምና መርጃ መሳሪያና ተያያዥነት ያላቸው ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት የተባበሩት አታሚዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና የፍ/ባለዕዳ ሲም የጥርስ ላብራቶሪ ሁለገብ የትምህርት ልማትና ህክምና መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/259911 በ24/6/2017ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/251729 በ01/04/2017 ዓ/ም በ24/6/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 446 ውስጥ የሚገኙ ፍርድ ያረፈባቸው የተለያዩ የጥርስ ህክምና መርጃ መሳሪያና ተያያዥነት ያላቸው ንብረቶች በባለሙያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 499,352 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠን ሺህ ሦስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር) ሆኖ በሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ23/11/2017 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4ኛ ብር 124,838 (አንድ መቶ ሀያ አራት ሽህ ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የተራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራችበሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታውአይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈዳ] ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት