የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከመስከረም 01 ቀን 2018 እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በየእለቱ ከሚታረዱት በጎች እና ፍየሎች የሚገኘውን እርጥብ ሌጦ እና ከዳልጋ ከብት የሚገኘዉን እርጥብ ቆዳ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com(Aug 20, 2025)

የዳልጋ ከብት ቆዳ እና የበግ ፍየስ ሌጦ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከመስከረም 01 ቀን 2018 እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በየእለቱ ከሚታረዱት በጎች እና ፍየሎች የሚገኘውን እርጥብ ሌጦ እና ከዳልጋ ከብት የሚገኘዉን እርጥብ ቆዳ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡-

ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡

  • ለዳልጋ ከብት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በወር ዉስጥ ለሚገኘዉ የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በስፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ለ10 ቀናት ብር 3,000,000.00 (ሦስት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መዉሰድ ይቻላል፡፡
  • ጨረታው ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *