Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ፣ የሰመራ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ እና ተያያዥ መገልገያዎች የእድሳት ፕሮጀክት የምህንድስና ዲዛይን ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ማማከር አገልግሎት ለሚሰጡ ደረጃ 1 የውጭ እና የአገር ውስጥ የህንጻ እና አጠቃላይ አማካሪ ድርጅቶችን (Category 1 International and local Building/General Consultants for the Detailed Engineering Design Review, Construction Supervision & Contract Administration of Semera Airport Terminal and Ancillary Facilities Renovation Project) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T563
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ፣ የሰመራ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ እና ተያያዥ መገልገያዎች የእድሳት ፕሮጀክት የምህንድስና ዲዛይን ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ማማከር አገልግሎት ለሚሰጡ ደረጃ 1 የውጭ እና የአገር ውስጥ የህንጻ እና አጠቃላይ አማካሪ ድርጅቶችን (Category 1 International and local Building/General Consultants for the Detailed Engineering Design Review, Construction Supervision & Contract Administration of Semera Airport Terminal and Ancillary Facilities Renovation Project) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ የአገር ውስጥ እና የውጭ አማካሪዎችን ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ፈቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ተመዝግበው የማማከር አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው እና በዘርፉ ለመስራት ለ2017 ዓ.ም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
4. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T563 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
6. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
7. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ማክሰኞ መስከረም 20/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የሠራተኞች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-4918
አሰፋ ኃይሉ
ኢሜይል፡ Assefah@ethioplanairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።