Your cart is currently empty!
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-A-02/2018
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፍቃድ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የቫት ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN No/ ሁሉም ንግድ ፈቃዶች በተናጠል ኮፒ መደረግ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግብር ስለመክፍላቸውና ጨረታ ለመሳተፍ የተፈቀደ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ማስረጃ ወይም ወርሃዊ የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉና ከሚመለከተው መስሪያ ቤት የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ሁኖ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND/ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት/ GUARANTEE ፡፡
ስለሆነም፡–
1. የተለያዩ አይነት የስራ አልባሳት ብር 10,166.79፤
2. የተለያዩ አይነት የቢሮ ፅህፈትና የስልጠና መርጃ እቃዎች ብር 62,269.86፤
3. የተለያዩ አይነት ቅርጻቅርጾች ህትመት ብር 9,465.65፤
4. የተለያዩ አይነት የታካሚ ቀለብ ብር 14,914.46፤
5. የተለያዩ አይነት የፅዳት እቃዎች ብር 58,099.85፤
6. የተለያዩ አይነት የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ብር 299,287.50፤
7. የዳቦ ማሽን እና የጀነሬተር መለዋወጫ እቃዎች ብር 40,153.30፤
8. የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ አላቂ መለዋወጫ እቃዎች ብር 16,750.33፤
ጨረታው ከዓርብ 16/12/2017 እስከ ረቡዕ 28/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሽጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ሐሙስ 29/12/2017 ዓም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ዋናው ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ.ም በሃገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማች አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ–ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር፡-058-321-2892/ 09-87-39-48-58
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ