በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ምስራቅ በር ቁ1 የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ምስራቅ በር ቁ1 የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት 

  • ሎት 1. ደንብ ልብስ
  • ሎት 2 ደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 3. አላቂ የቢሮ እቃ
  • ሎት 4. ህትመት
  • ሎት 5. የህክምና እቃዎች
  • ሎት 6. አላቂ የትምህርት እቃ
  • ሎት7 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 8. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
  • ሎት 9. ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና
  • ሎት 10. ለስልጠና ግብዓት
  • ሎት 11. ለፕላንት ማሽነሪ እቃ
  • ሎት 12 ለተገጣጣሚ ቋሚ እቃ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ተመዝግበው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
  5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

የሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

 

የተጠበቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1

ደንብ ልብስ

 

8000 (ስምንት ሽህ ብር)

 

ሎት2

ደንብ ልብስ ስፌት

 

1000 (አንድ ሽህ ብር)

 

ሎት3

አላቂ የቢሮ እቃ

 

4000 (አራትሽህ ብር)

 

ሎት4

ህትመት

 

2000 (ሁለት ብር)

 

ሎት5

አላቂ የህክምና እቃ

 

3000 (ሶስትሽህ ብር)

 

ሎት6

አላቂ የትምህርት እቃ

 

8000 (ስምንት ብር)

 

ሎት7

አላቂ የጽዳት እቃዎች

 

7600 (ሰባት ሽህ ስድስት መቶ ብር)

 

ሎት8

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

 

3000 (ሶስት ሽህ ብር)

 

ሎት9

ማሽነሪ ጥገና

 

1000 (አንድ ሽህ ብር)

 

ሎት10

የስልጠና ግብአት

 

1000 (አንድ ሽህ ብር)

 

ሎት11

ለፕላንት ማሽነሪ እቃ

 

5200 (አምስት ሽህ ሁለት መቶ ብር)

 

ሎት12

ለተገጣጣሚ የቢሮ እቃዎች

 

5200 (አምስት ሽህ ሁለት መቶ ብር)

 

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ሲያሸንፉ የውል ማስከበርያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርቡዋቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ አማራጭ ናሙና ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡

11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት በት/ቤቱ ንብረት ክፍል ግቢ ማድረስ አለበት፡፡

12. የተለያዩ እቃዎችን አንድ የዋጋ ዝርዝር ላይ የተለያዩ እቃዎች ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ምስራቅ በር ቁ1 የመጀ/ደ/ት/ቤት