የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለም ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/ST/129/2025

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለም ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የዕቃውን ዓይነት

 

የፕሮጀክት ስም

 

የጨረታ ቁጥር

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

 

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

 

የጨረታ ማስከበሪያ

 

የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለም

 

ለዋና /ቤት

 

DCE/ ST/129/2025

 

ነሀሴ 28 ቀን 2017 .400 ሰዓት

 

ነሀሴ 28 ቀን 2017 .415 ሰዓት

 

20,000.00

 

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
    አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mall አድራሻ lnfo@dce-et.com 
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com 
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.0114-40-04-71/0114-42-07-46
 የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *