Your cart is currently empty!
የባንቱ ሆስፒታል የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ አላቂ እቃዎች፣ እስቴሽነር፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፤ ለህሙማን አገልግሎት መስጫ ካርዶችና የህትመት ውጤቶች፤ የመኪና ጎማ ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የባንቱ ሆስፒታል የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ አላቂ እቃዎች እስቴሽነር የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፤ ለህሙማን አገልግሎት መስጫ ካርዶችና የህትመት ውጤቶች ፤የመኪና ጎማ ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ኮፒውና ኦርጅናሉን በማቅረብ ስም ፤ ፈርማና አድራሻቸዉን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነድ ከተገለፀው የዕቃ ፕሮፖዛል ውጭ ተመሳሳዩን ማቅረብ እንደማይቻልና ደረጀውን ያልጠበቀ ዕቃ በስህተት ቢቀርብ መቀየር የሚችል፡፡
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጃው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በሆስፒታሉ አዳራሽ ይከፈታል
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) 5000.00/አምስት ሺህ/ ወይም በካሽ ከጨረታዉ ሠነድ ጋር ብር 5000.00/አምስት ሺህ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸዉ ከተረጋገጠ በኋላ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈው 10% ማስያዝ አለበት
- ያሸነፈውን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠና ዕቃውን ጽ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ አምጥተው ካስረከቡ በኋላ ክፍያው ይፈፀማል፡፡
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ ከባንቱ ሆስፒታል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር (suppliers list) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድረሻችን የቶሌ ወረዳ ፤ በሰበታ-አስጎሪ-ባንቱ መስመር ከኢ.አ 8 ኪሜ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0929 477 313/0930 441 009/0922 733 196/0922 392 444/ መደወል ይችላሉ፡፡
በደ/ምዕ/ሸዋ ዞን የባንቱ ሆስፒታል
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Electrical, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx