Your cart is currently empty!
የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አብይ ሰይፈ ወ/ጊዮርጊስ እና በፍ/ባለዕዳ አይዳ ደስታ ገ/መድኅን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.85538 በቀን 27/06/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.102296 በቀን 14/09/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጉለሌ ክ/ከተማ በቀድሞው ቀበሌ 01 በአሁኑ አደረጃጀት ወረዳ 08 የቤ.ቁ.አዲስ በእነ ወ/ሮ መዓዛ ወ/ማሪያም በሚል መለያ ቁጥር AA000100803570 ጂ + 2 የቦታ ስፋት 250 ካ/ሜ የቤት ስፋት 324.15 ካ/ሜ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 14,648,500 (አሥራ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት