Your cart is currently empty!
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ካፍቴሪያዎች የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት ብቃት ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የካፍቴሪያ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር
ት.መ.ማ.ማ.ድ/NCB/05/2017
ድርጅታችን – በድርጅቱ ውስጥ ለሚገኙት ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ካፍቴሪያዎች የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት ብቃት ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሁለቱም ካፍቴሪያዎች የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግደታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ Tel /0116 -46-34 81 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት