Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከአዘዞ-ጐንደር እያከናወነ ላለው የመንገድ ግንባታ አንድ (1) ባክ ሎደር መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የማሽን ኪራይ ጨረታ ቁጥር GN-004/2018
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከአዘዞ-ጐንደር እያከናወነ ላለው የመንገድ ግንባታ አንድ (1) ባክ ሎደር መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ለዘርፉ አግባብነት ያለው የተመዘገበ የንግድ ፈቃድ
- ከግብር ዕዳ ነፃ በመሆናቸው በጨረታ እንዲሳተፉ የተሰጠ ክሊራንስ
- የቫት ምዝገባ ሠርተፌኬት
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ማስረጃ
- የማሽን ባለቤትነት ማስረጃ (ሊብሬ) ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ያላቸው
- ባክ ሎደሩ የስሪት ዘመኑ እ.ኤ.አ ከ2012 በኋላ የሆነ
- የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና የብር 20,000 CPO ማስያዝ እና ብቁ ኦፕሬተር ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን: ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲስትሪክቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው ፎርም በመሙላትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ከላይ የተመለከቱትን የህጋዊነት ማስረጃዎች በሌላ ፖስታ በማሸግና ሁለቱን ፖስታዎች እንደገና በአንድ ላይ በማሸግ የኢመአ ዋናው መ/ቤት ወይንም የኢመአ ጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-664 988/0925-356 890 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
ማሳሰቢያ ዝርዝር ሁኔታዎች በኢትዮጵያ መንግስት ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሠረት የሚፈረም ሲሆን፣ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርሙን በዲስትሪክቱ ጽ/ ቤት ግዥ እና አቅርቦት ቡድን ቢሮ ማግኘት ይቻላል። መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት