የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የመኪና ጎማዎች፣ ስፔርፓርት እና ባትሪ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ ጨረታ

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት /እቃ/ ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች
  • ሎት 2 የተለያዩ የመኪና ስፔር ፓርት
  • ሎት 3 የተለያዩ የመኪና ባትሪ

በዚሁ መሠረት ከላይ ለተገለፀው ግዥ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ ዓይነት በዘርፉ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀቶች፣ በአቅራቢነት ድረ-ገፅ (Web Site) ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸው ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንዲሣተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች የእያንዳንዱን የሚወዳደሩበትን ጨረታ ሠነድ ላይ የተገለጸውን የዕቃውን /የአገልግሎት/ ዝርዝር መግለጫ መሠረት በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በሎጀስቲክስና ፕሮኪዩርመንት ዳይሬክቶሬት ብሎክ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒዎችን ለየብቻው በትልቅ ፖስታ በማሸግና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በኮርፖሬሽኑ ስም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው።
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለተጨማሪ መረጃ ኮርፖሬሽኑ የሚገኘው 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ሆቴል ገባ ብሎ ብሎክ ቁጥር 3 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0938724589 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *