Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳ ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳ ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውንና 2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ የ2018 ያደሱ፡፡
- ተጫራቾች የእቃ አቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከአደራጃቸው ድርጅት የዋስትና ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር አንድ (1) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ ታሽጎ በኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው በ 02/01/2018 ዓ.ም ከ7፡30 እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ በቢሮ ቁጥር አንድ (1) ገቢ ማድረግ አለባቸው። ጨረታው በዚው ዕለት በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ሚኤሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ቅጥር ግቢ የሚገኘው መጋዘን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ብዛትና ጥራት አሟልተው ግዴታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሽያጭ የቀረበውን ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ/ ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
- የማስጫኛና የማስወረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉት ሰነድ ስርዝ ድልዝ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መኖር አለበት፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ውሉን ከተፈራረሙ በኋላ ዋጋው የፀና ይሆናል፡፡
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 09-67-73-87-07
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት