Your cart is currently empty!
በልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 05 አስተዳደር የእድገት በሥራ የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ቁጥር /01/2018ዓ.ም
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ እና የሥራ ልብስ ….. የጨረታ ማስከበሪያ 400 ብር።
- ሎት 2.ልዩ ልዩ የፅዳት እቃዎች…የጨረታ ማስከበሪያ 3500 ብር በመክፈል።
- ሎት 3.አላቂ የቢሮ እቃዎች…የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመክፈል።
- ሎት4.ልዩ ልዩ መሳሪያዎች መግዣዎች ….የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል።
- ሎት 5.ለፕላንት እና ማሽነሪ መግዣ …… የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመክፈል።
- ሎት 6. አላቂ የትምርት እቃዎች…የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመክፈል።
- ሎት 7.ለፕላንት እና ማሽነሪ እድሳት ጥገና………የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል።
- ሎት 8.ለሕንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች ግዥ ……የጨረታ ማስከበሪያ 2000ብር በመክፈል።
- ሎት 9. ለህትመት ሥራዎች………. የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል።
- ሎት 10. ልዩ ልዩ የህክምና እቃዎች ……የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ እድገት በሥራ የመጀ/ደ/ት/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሰት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲን እና የቫት ተመዘጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ልደታ ክ/ከተማ እድገት በሥራ የመጀ/ ደ/ት/ቤት የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡ እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት እድገት በሥራ ት/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ሳጥን በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል (ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ድረስ)
- ት/ቤቱ(መስሪያ ቤቱ) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- የዘገየ ጨረታና በመክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- ዋጋ ሲሞሉ ቫትን አካተው ይሙሉ(ያቅርቡ)፡፡
አድራሻ፡ ልደታ ክ/ከተማ እድገት በሥራ የመጀ/ደ/ት/ቤት ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ሞሀ ለስላሳ ፊት ለፊት ስልክ፡– 011 515 7055
በልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 05 አስተዳደር የእድገት በሥራ የመጀ/ደ/ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Materials cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx