በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ሊገዛቸው ያቀደውን የተለያየ ዓይነት ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግልጽ ጨረታ በማውጣት መስፈርቱን ከሚያሟሉ ድርጅቶች የሚፈለጉ ዕቃዎች እና አገልግሎቶቹ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግ/ጨ/ቁ/01/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ሊገዛቸው ያቀደውን የተለያየ ዓይነት ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግልጽ ጨረታ በማውጣት መስፈርቱን ከሚያሟሉ ድርጅቶች የሚፈለጉ ዕቃዎች እና አገልግሎቶቹ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

.

 

የጨረታው ዓይነት ዝርዝር

 

ለጨረታ ማስከበሪያ

 

ምርመራ

 

ሎት 1

የህትመት ሥራዎች

 

20,000

 

ናሙና መቅረብ አለበት

 

ሎት2

የማስታወቂያ ሥራዎች

 

20,000

 

 

ሎት3

ሳውንድሲስተም መድረክ ዝግጅት እና ላይትኒንግ

 

20,000

 

 

ሎት4

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

20,000

 

ናሙና መቅረብ አለበት

 

ሎት5

የስቴሽነሪ እቃዎችና የፕሪንተር ቀለሞች

10,000

 

ናሙና መቅረብ አለበት

 

  1. ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ የንግድ ሥራ ምዝገባ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የአቅራቢዎች ዝርዝር እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ሰሜን ጀግኖች በር ቢሮ ቁጥር 6 ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ስም በማሠራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን/የሥራውን⁄ ዓይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍ ፋይናንሻልና ቴክኒክ በተለያየ 2 ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ሰሜን ጀግኖች በር ቢሮ ቁጥር 6 ግዥ ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ሰሜን ጀግኖች በር በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ አዳራሽ ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  6.  ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ