Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ መምሪያ በ7ቱም ክፍለ ከተሞች ውስጥ ለሚያለማው 39 ሎት አረንጓዴ ልማት ማንከባከብ ስራ በስራ መስኩ ከተደራጁ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ማህበራትን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ መምሪያ በ7ቱም ክፍለ ከተሞች ውስጥ ለሚያለማው 39 ሎት አረንጓዴ ልማት ማንከባከብ ስራ በስራ መስኩ ከተደራጁ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ማህበራትን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ. (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፤ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በመያዝ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፤ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ2% በላይም ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበው መሀንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ5% በላይ ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበው መሀንድስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከ15% በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ስራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ ዋጋ ትንተና (Direct unit cost analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን ውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-220–99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መም/ያ
ሀዋሳ