Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም የጽህፈት መሣሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር በሥሩ ለሚተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከሎት 01/2018 እስከ ሎት 02/2018 ያሉት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች፡-
- የጽህፈት መሣሪያ፡- ሎት/ምድብ 01/2018
- የጽዳት ዕቃዎች፡- ሎት/ምድብ 02/2018
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛትይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 046-220–99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መም/ያ
ሀዋሳ