የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ቁሳቁስ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 01/2018

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ቁሳቁስ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣ ጨረታ መሳተፍ የሚችልና የምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል/የሚትችል።
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15(አስራ አምስት ቀን) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸው አማካይነት መግዛት ይቻላል።
  3. በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Bond) ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና/Bank Guaranty/ ወይም የክፍያ ማዘዣ(CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
  4. አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
  5. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ኬዝ ቲም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
  9. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
  10.  የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  11.  በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916 108 360/0916 070 057 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- ጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ/ብ/ክ/መ/እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *