የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ንብረትነቱ የልማትና ሆቴል ማህበር (አ.ማ) የሆኑ አገልግሎት የሰጡ ቴሌቪዥኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2025

የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ንብረትነቱ የልማትና ሆቴል ማህበር (አ.ማ) የሆኑ አገልግሎት የሰጡ ቴሌቪዥኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ፎርም ከአዲስ አበባ ሒልተን ኢንተርናሽናል ሂሳብ ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡ 

  • ለጨረታ የሚቀርብ ማንኛውም ተወዳዳሪ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ሆኖ ፈቃዱም በ2017 ዓ. ም የታደሰ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ቴሌቪዥኖቹን ከነሐሴ 19 ቀን እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ. ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ብቻ የጨረታ ሰነዱን እየገዙ ማየት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት መነሻ ሰዓት 4፡00 ሰዓት ብቻ በመሆኑ ከ4፡00 ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች እንደማንቀበል በቅድሚያ እናሳውቃለን፡፡
  • ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ነሐሴ 23 እና ነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ብቻ ሒልተን አዲስ አበባ ዳይሬክተር ኦፍ ፋይናንስ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ / በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ./ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲ.ፒ.ኦ. ያልቀረበበት እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ከጨረታው ውጭ ይሆናል/፡፡
  • ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ. ም ከጠዋቱ በአራት ሰዓት ተኩል (4፡30) ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ሒልተን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አሸናፊውን ካሳወቅን ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ ዕቃውን በሙሉ ማንሳት አለበት፡፡

ሒልተን አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *