የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅታችን በላይኛው ግቢ በአዲሱ ፍልውሃ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ክፍት ቦታ የሆቴሉን ህግና ደንብ የሚያከብሩ ህጋዊ የስጋ ንግድ ፍቃድ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በማከራየት ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅታችን በላይኛው ግቢ በአዲሱ ፍልውሃ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ክፍት ቦታ የሆቴሉን ህግና ደንብ የሚያከብሩ ህጋዊ የስጋ ንግድ ፍቃድ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በማከራየት ማሰራት ይፈልጋል።

 በዚህም መሠረት

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የቦታ ኪራይ /የአገልግሎት ግዥ

  • ሎት 1 የስጋ ቤት ኪራይ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ IN እና VAI ሰርተፊኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 የግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25.000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነድን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንሙሉ አድራሻቸውን፤ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ ፣ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለፅ አለበት።
  7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
  8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባቸኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው ፋይናንሻል ዋጋ ሠነድ ለብቻው እና ሲፒኦ /CPO/ ለብቻ በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት1 ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ1ዐዐ% አሸናፊ የውለታ ሂደቱ ይፈፀማል፡፡ ነገር ግን ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስረከቢያ (CPO) ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሠነድ ደግሞ ሉበቻው ታሽጎ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባ አለባቸው፡፡
    ተጫራቾች ቴክኒካል ግምገማ 60% መገምገሚያ መስፈርቶች እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

11.1 የቀረበው ሰነድ በተጠየቀው መሠረት ስለመሆኑ 25%

11.2. የድርጅቱ የሥራ አፈፃፀም ወይም የሥራ ልምድ 15%

11.3. የማቅረቢያ ጊዜ 15%

11.4. የሰነድ ዝግጅት 5%

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- 011 553 0767 / 011 515 7337

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *