Your cart is currently empty!
ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር እና እህት ድርጅቶች የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ዕቃ ለመግዛት የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር እና እህት ድርጅቶች የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሙሉ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነድ ያገኛሉ።
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መረጃዎች፡-
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበትን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ ክሊራንስ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ እና በግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የአቅራቢነት ማስረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትንና እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆኑን መገለጽ አለበት፡፡ የታክስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጪ አካቶ እንደተሞላ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር 10,000 ብር(አስር ሺህ ብር) በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ፋይናንሺያል ኦርጅናል ሰነድ ፖስታ ውስጥ አብረው በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በሀዋሳ ከተማ በገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው ዳዬ በንሳ ህንጻ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር—ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡20 እስከ 4፡30 ድረስ በቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን አስገብተው ጨረታው በዕለቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾት የሚያቀርቡት ዋጋ ቢያንስ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚሆን መሆኑን መገንዘብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የፋይናንሺያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ከጨረታም ያሰርዛል።
- የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አ/አበባ ሮቤራ ቡና ፊት ለፊት በሚገኘው ፒስታ መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግል ማህበር
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 251 116675551/0944350296
ዳዬ በጓሳ ቢዝነስ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር