በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና እቃ መለዋወጫዎች(ፋስት ሙቪንግና ሌሎች እቃዎች) እና የመኪና ጎማ አመታዊ ኮንትራት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 25, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት1. የመኪና እቃ መለዋወጫዎች(ፋስት ሙቪንግና ሌሎች እቃዎች) አመታዊ ኮንትራት ግዥ
  • ሎት 2. የመኪና ጎማ አመታዊ ኮንትራት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው። 
  4. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30ሰዓት ድረስ በማስገባት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅደም ተከተል በስራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል።
  7. በጨረታው ለመጫረት የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር -033-450-02-22 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጎልም።
  9. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  10. ውድድሩ የሚካሄደው ሎት1 እና ሎት 2 በየምድቡ በሎት ነው።
  11. የእቃው ማስረከቢያ ቦታ ሎት 1 እቃዎች መኪኖች ለጥገና አገልግሎት ጋራጅ በሚገቡበት ጊዜ የጥገና አገልግሎት በሚሰጠው ጋራጅ በመገኘት በባለሙያና በጋራጅ የተረጋገጠ ኦርጅናል _ እቃ ለንብረት ክፍል የሚያስረክብ ይሆናል እንዲሁም ሎት 2 መቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡ በተጨማሪም እቃዎች በሚፈለጉበት ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *