Your cart is currently empty!
በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያየ መጠን ያላቸዉን ኤዲፒ ዌልዲንግ ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Aug 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማችን ለመጠጥ ዉሃ የተዘረጋዉን የዉሃ መስመር መበየጃ አገልግሎት የሚዉሉ
- የተለያየ መጠን ያላቸዉን ኤዲፒ ዌልዲንግ ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የእቃው (የግንባታው) ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ - ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/ አሰተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤ ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና
አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ - የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት ተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በጽ/ቤቱ በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት ሲሆን፤ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በጠቅላላዉ ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፈባቸዉን እቃዎች በራሱ ወጭ ዱርቤቴ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ አቃዎች (አገልግሎቶች) ዓይነትና ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎች እና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው ቀርበዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር. 058 223 08 16 /09 74 50 58 99
በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት