በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚንስቴር በታክስ ዕዳ የተያዙ የመኖሪያ ቤት፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በታክስ ዕዳ የተያዙ የመኖሪያ ቤት፣ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተያዩ ንብረቶችን

መሸጥ የወጣ ልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ 01/2017

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚንስቴር ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታከስ ዕዳ በታ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምከንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ለገዳዲ ለገጣፎ ከተማ ላይ ያለ 500. ላይ ያረፈ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ መኖሪያ ቤት፣ ከሜጋ ቪሌጅ ሪልእስቴት /የተ/የግ/ማህበር የኮንስትራክሽን እቃዎች (እስካፎልዲንግ) ከፎኔክስ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበር (የፕላስቲክ ገመድ መጠቅለያ ማሽን) ከኡኑፕሬሳ ኮንስትራክሽን እና ከሰንራይዝ ስቲልነስ ፕሮዳክሽን /የተ/የግ/ማህበር (ኮምፒውተር ፕሪንተር እና የመቁረጫ ማሽኖች) ፣ከፒጂኤ ቴከ /የተ/የግ/ማህበር፣ ከሜትሮ ኮሚኒኬሽን /የተ/የግ/ማህበር፣ ከሲቲ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ፣ ከፓትሮል የጥበቃ አገልግሎት፣ ከጄቢ ኮንስትራክሽን /የተ/የግ/ማህበር እና ከአቶ ተክኤ ዘርአይ /መድህን የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን 6 ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡

1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት)ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት ህንፃ” 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ” 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚንስቴር ስም (Ministry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በሚከተሉት የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡

.

የመስሪያ ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ገቢዎች ሚንስቴር

ለገጣፎ ከተማ በካርታ ቁጥር ORO42012004005 ተመዝግቦ የሚገኝ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ መኖሪያ ቤት ፣ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ የመቁረጫ ማሽኖች ፣፣የፕላስቲክ ገመድ መጠቅለያ ማሽን እስካፎልዲንግ እና የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች

ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት እና 30 ቀናት

የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች አስካ ፎልዲንግ፣ የፕላስቲክ ገመድ መጠቅለያ ማሽን፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የመቁረጫ ማሽኖች ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን 345 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 400 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን የመኖሪያ ቤቱ ጋዜጣው በወጣ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ 31ኛው ቀን 345 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 400 ሰዓት ይከፈታል

5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡መገናኛ በሚገኘው በሚንስቴር /ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ፡፡

6. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡

7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ /ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ከላይ በተ/ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚንስቴር /ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

11. ሚንስቴር /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-8490 ኮድ(2044)(2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *