በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ትም/ቢሮ ቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዘመን የኔትወርክና ኮምፒውተር መለዋወጫዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የህንጻ ጥገና ዕቃዎች፣ ህትመት፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ጥገናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ//////ትም/ቢሮ ቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ 2018 የበጀት ዘመን ለኮሌጁ ትም/ ስራ አገልግሎት የሚውሉ፡

  1. የኔትወርክና ኮምፒውተር መለዋወጫዎች
  2. የጽህፈት መሳሪያዎች
  3. የጽዳት ዕቃዎች
  4. የተለያዩ የህንጻ ጥገና ዕቃዎች
  5. ህትመት
  6. የመኪና ጎማ
  7. የመኪና ጥገናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦

  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
  • ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  • የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
  • ሌሎች በተጫራች መመሪያ /ቤቱ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ
  1. ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን ዝርዝር የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ከኮሌጁ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ከፍል መውሰድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈልና ዋጋ በመሙላት መወዳደር ይችላሉ
  2. ተጫራቾች የዕቃ ዋጋ ከሞሉ በኋላ ለጨረታው ማስከበሪያ የጨረታውን ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
  3. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 16 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 2፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ጨረታ ክፍል ይከፈታል 16ኛው ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል
  5. በጨረታ ሳጥን አከፋፈት ወቅት ሥነስርዓት ላይ ተጫራቾች አለመቅረብ የጨረታው አከፋፈት አያስተጓጉልም
  6. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች እስከ ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት
  7. /ቤቱ ለዕጩ ተጫራቾች በጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ላይ የገለጻቸው የጨረታ ስነስርዓቶች፣ መስፈርቶችና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከገለጻቸው የሚለዩ ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የገለጻቸው የበላይነት ይኖራቸዋል
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የተጫራች መመሪያ አብሮ መያያዙን ማረጋገጥ እና መመሪያውን መከተል ይኖርባቸዋል
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማንኛውም የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው በወጣበት ቋንቋ መሆን ይጠበቅበታል
  10. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

በደ///////ቢሮ

ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ