Your cart is currently empty!
የቤቱ ስፋት 41.2 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለሙበት አቶ ታደሰ ደበበ እና በፍ/ባለዕዳዎች እነ ያሬድ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.273254 በቀን 2/2/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.301864 በቀን 16/4/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 በአሁኑ አዲስ ከተማ ከ/ከተማ ወ12 ውስጥ የሚገኝ የቤ/ቁ 320 የሆነ በካርታ ቁጥር ወ/12/ወዝ01/669/15271/0 በይዞታ መለያ ቁጥር AA000091201251 በእነ አዳነች ሹሜ በርሄ ስም የተመዘገበ የተነጻጻሪ ካርታ ያለው ሲሆን የቤቱ ስፋ 41.2 ካ/ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታው ስፋት 36.88 ካ/ሜ ጠቅላላ የቦታው ስፋት ከቀበሌ ቤት ጋር 170 ካ/ሜ የሆነ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,047,771.52 (ሶስት ሚሊዮን አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አንድ ከ52/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቄንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት