Your cart is currently empty!
የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የእህል ተባይ ማጥፊያ መድሃኒት ሴልፎስ እና ማላታይን እንዲሁም ለመኪኖች አገልግሎት የሚውል ጂፒኤስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 30, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የእህል ተባይ ማጥፊያ መድሃኒት ሴልፎስ እና ማላታይን እንዲሁም ለመኪኖች አገልግሎት የሚውል ጂፒኤስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጸለን፡፡
ስለሆነም:-
1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number)ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
2. የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
4. ስለ ሚገዛው እቃ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
5. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት እስከ 15ተኛዉ ተከታታይ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ/መግዛት/ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሪ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፣
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን አለበት፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ በሆኑ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተገለጸው ቦታ ቀን እና ሰዓት መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10, ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ትልቁ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀስው ሰዓት ይከፈታል፡፡ተጫራጮች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 105 እና 108 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 0014/ 058 218 1103 በመደወል ማግኘት ይቻላሉ።
የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን